የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመሬት ዝርፍያ ጋር በተያያዘ ሲያደርገው በቆየው የማጣራት ስራ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚን ጨምሮ፤የክ/ከተማ በመሬት ጉዳይ ይወስኑ የነበሩ አመራሮች ፤ ባለሙያዎች ፤ ደላሎችና ከህብረተሰቡ ውስጥ በዚህ ድርጊት የተሳተፉትን ጨምሮ 37 ሰዎችን በመለየት ለህግ እንዲቀርቡ እንቅስቃሴ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ 12 ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል፡፡
ቀሪዎቹን ግለሰቦችም ፖሊስ ክትትል እያደረገባቸው ይገኛል፡፡ ተጨማሪ የማጥራት ስራም ተጠናክሮ ቀጥሏል::
በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦችም:-
1. ለምለም አባይነህ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ዋና ስራ አስፈፃሚ
2. አቶ ከፍያለው አሰፋ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የፕሮሰስ ካውንስል አመራር የነበሩ (በመሬት ጉዳይ ውሳኔ የሚሰጡ የነበሩ)
3. አቶ ዋሲሁን ሰውነት የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የፕሮሰስ ካውንስል አመራር የነበሩ (በመሬት ጉዳይ ውሳኔ የሚሰጡ የነበሩ)
4. አቶ ኢብራሂም ሀሰን የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የፕሮሰስ ካውንስል አመራር የነበሩ (በመሬት ጉዳይ ውሳኔ የሚሰጡ የነበሩ)
5. አቶ ሃይለየሱስ ደስታ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የፕሮሰስ ካውንስል አመራር የነበሩ (በመሬት ጉዳይ ውሳኔ የሚሰጡ የነበሩ)
6. አቶ ዳዊት ከልሌ የቴክኒካል ካርታ ዝግጅት ባለሙያ
7. አቶ ልኡልሰገድ ታደሰ የቴክኒካል ካርታ ዝግጅት ባለሙያ
ከመንግስት ተቋማት ውጪ በጉዳዩ ተሳታፊነት በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች
8. አቶ አየለ ጉቱ
9. አቶ ጎሳዬ ደሜ
10. አቶ በፍቃዱ ወንደሰን
11. አቶ ሮባ ደበሌ
12. አቶ መታሰቢያ አባተ ናቸው፡፡