በ69 ቀናት ተገንብቶ የተጠናቀ ህንፃ

 

በ69 ቀናት በሃገራችን የምህንድስና የእድገት ደረጃ አዲስ ታሪክ የተፃፈበት ፈጣኑ ህንፃ ዛሬ የመጨረሻው ማደማደሚያ ጣሪያ ተመቷል፡፡

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ልዩ ድጋፍ ሲያደርጉ በቆዩበት በቂርቆስና በልደታ ክ/ከተሞች በ60 /90 ቀናት ፕሮጀክት ተጀምረው የነበሩት ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የሚጠቀሙት ባለ 11 ባለ 9 እና ባለ 5 ወለል ህንፃዎች ለከተማችን አዲስ አሻራ አዲስ ታሪክ እና አዲስ የስራ ባህልን እያስመዘገቡ ነው፡፡

እነሆ የዚሁ ፕሮጀክት አካል የሆነው በቂርቆስ ክ/ከተማ ሲገነባ የቆየው ባለ 9 ወለል ህንፃ በዛሬው እለት በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ የመጨረሻውን ወለል ጣሪያ በመምታት ውብ በሆነ መንገድ ማጠናቀቅ የተቻለ ሲሆን አዲስ ታሪክም ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ፈጣኑን ቴክኖሎጂ እየተገበረ ያለው ይህ ፕሮጀክት የኩምካንግ አልሙኒየም ፎርምወርክ ቴክኖሎጂ (KumKnang Aluminum formwork technology) በመባል የሚታወቀውን የተለመደውን የኮንስትራክሽን ሂደት እጅግ ባሳጠረ መንገድ የሚተገበር ድንቅ ቴክሎኖጂ ነው፡፡

ልስን ቁርቋሮ ማፅዳት ትራንስፖርት የሚባሉ ጣጣዎችን በሙሉ በማስቀረት የሚተገበረው ይህ ስራ የከተማችንን የቤት ጥያቄ ለመመለስና በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤት ለማምጣት እንደሚቻል ትክክለኛ ማሳያ ሆኖ የሚያገለግል ነው፡፡

አዲስ ታሪክ አዲስ አሻራ፤ ብፅግናችን በአዲስ የለውጥ መንፈስ ከግቡ ይደርሳል!!

#አዲስአበባ_የብልፅግና_ተምሳሌት

Share this Post