በአዲስአበባ የ8ኛ ክፍል ፈተና ዛሬ ተጀምሯል

"በአዲስአበባ የ8ኛ ክፍል ፈተና ዛሬ ተጀምሯል። ፈተናው ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ፈተናውን እየወሰዱ ከሚገኙ ከ71 ሺህ 832 ተማሪዎች ውስጥ የየመንና የሶርያ ስደተኞችም ይገኙበታል።

ለሁሉም ተማሪዎች መልካም እድል እመኛለሁ ።ፈተናዉ በተረጋጋና ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ እንደተጀመረዉ ሁሉ፣ እስኪጠናቀቅ ባለድርሻ አካላት ፣መምህራንና ተማሪዎች እንደወትሮው ሁሉ በትጋት ሀላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪዬን አቀርባለሁ ።

በድጋሚ መልካም እድል !"

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

Share this Post