12
Jan
2024
ወንጪ ሁሌም ንፁህ የተፈጥሮ ስጦታ ሆና ቆይታለች። የተፈጥሮን ድንቅ በረከት ተቀብሎ ተንከባክቦ እና አበልፅጎ መጠቀም ደግሞ የኛ የሰውልጆች ተጠባቂ ተግባር ነው።
የወንጪ ዳንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደርን በማልማት ሂደት በግንባታው ምዕራፍ ከ8,000 እስከ 12,000 ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል። ግዙፍ የመሰረተ ልማት ስራ ተሰርቷል።
43 ኪ.ሜትር መንገዶች፤ 35ኪ. ሜትር የመንገድ መብራት እና የኃይል አቅርቦት፤ 72 ሜትር ድልድይ እና ትምህርት ቤት ተጠቃሽ ናቸው። የአካባቢው ወጣቶች ታላላቅ የልማት ስራዎች ይዘው የሚመጡትን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማጣጣም ጀምረዋል። ሰፊው የአካባቢው ማኅበረሰብም አሁን የላቀ የተጠቃሚነት ዕድል አግኝቷል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
ለተጨማሪ መረጃ፦
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCagI4q5d_EtvTsajRXWnFjA
Tik Tok= https://www.tiktok.com/@aacommu
Telegram https://t.me/AAcommu
Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=100066583024934...
Website https://cityaddisababa.gov.et