101 ለሚሆኑ የልማት ጥያቄዎች 74.76 ሄክታር መሬት ሕዝባዊ ጠቀሜታቸውን በመለየት በካቢኔ ውሳኔ በምደባ ምላሽ እንዲያገኙ ተደርጓል።
ለሆስፒታል ግንባታ 24 ቦታዎች ➪ ለሆቴል 12 ቦታዎች
ከኤምባሲዎች በልዩ ልዩ ምክንያት ተነጥቆ የነበረን 15 ቦታ እንዲመለስላቸው መደረጉ
የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርና ኢንቨስትመንትን በሁለቱ አገራት መካከል ለማሳደግ በማሰብ ለቻይና የባህል ማዕከልና ለቀርቃሃ ሰርቶ ማሳያ የሚሆን በድምሩ 2 ቦታዎች መስጠት መቻሉ
ልዩ ልዩ ሕዝባዊ ጠቀሜታ ላላቸው ኢንዱስትሪዎች 16 ቦታዎችን
ለባንኮች የግንባታ ቦታ ➪ ለትምሕርት ተቋማት 2 ቦታዎችን
የከተማችንን የቤት ፈላጊዎች ተደራሽ ለማድረግ እንዲቻል ለሪል እስቴት አልሚዎች 6 ቦታዎችን
በአጠቃላይ በ2013 በጀት ዓመት ማስተናገድ ከተቻለውን የመሬት አቅርቦት ጥያቄን ባካተተ መልኩ መሬት ማቅረብ ተችሏል።
ከዚሁም ጋር በተጓዳኝ 13 ሄክታር መሬት ለጨረታ ለማቅረብ የቅድመ ዝግጅት ስራም ተጠናቋል ።
በሕገ ወጥ መንገድ በወረራ የተያዘ 383.3 ሄክታር መሬት በማጣራት ለመሬት ባንክ ተመላሽ ማድረግ እንዲሁ ተከናውኗል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ለማስወገድ ብሎም የመሬት ዝርፊያን በተመለከተ ተጠያቂነትን ለማስፈን በርካታ አበረታች ተግባራትን ማከናወን ተችሏል:
አስቀድሞ ባልተገባ አግባብ የተሰራጨን ካርታን በማምከን ከ450ሺ በላይ የመሬት ካርታን በአዲስ መልክ እንዲቀየር በማድረግ በፎርጂድ ሲታተም የነበረን የመሬት ካርታን ማስቆም ተችሏል።
በአርሶ አደሮች ስም በደላሎችና ፣ማንነታቸው ለግዜው ባልተረጋገጠ አካላት የወጣን 2 ሺ 170 ካርታ በማጣራት 497 ይዞታዎች (207 ሺ ካሬ ሜትር መሬት)በሕገ ወጥ መንገድ እንዲያዙ የተደረጉ መሆኑ በመረጋገጡ እርምጃ መውሰድ ተችሏል ።
በሕገ ወጥ የመሬት ወረራ የተሳተፉ በከተማ አስተዳደር እስከ ወረዳ ባሉ መዋቅሮች የሚሰሩ 243 አመራሮችና ሠራተኞች ( 155 የመንግሥት የስራ ኃላፊዎችና 88 ባለሙያዎች) ላይ ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል።
መሬት ውስንና ቁልፍ ሃብታችን በመሆኑ ይህንን ውስን ሃብት በአግባቡ ለማስተዳደር የአሰራር ሥርዓተን ማሻሻል ፥ ዘመናዊ አገልግሎትን መዘርጋት ፥ ተጠያቂነትን ማስፈን ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ነው