የቂርቆስ ክ/ከተማ አስተዳደር በ90 ቀናት በልዩ ሁኔታ የሚተገበሩ እቅዶችን ከባለሃብቶች ፤መንግስታዊ ተቋማትና፤ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በዛሬው እለት ውይይት አደረገ፡፡

የቂርቆስ /ከተማ በሚቀጥሉት 90 ቀናት በልዩ ሁኔታ የሚተገበር እቅድ ይፋ አድርጓል፡፡ የዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚሆኑባቸው መኖርያ ቤት ፕሮጀክቶች ፤የቤት እድሳት ፤ለወጣቶችና ለሴቶች የስራ እድል የሚፈጥሩ የመስርያ ቦታዎች ፤የዳቦ ፋብሪካ ፤ፓርኮች፤የከተማ ግብርና የመሳሰሉት የእቅዱ አካላት ናቸው፡፡

በስነስርዓቱ ላይ የተገኙት ባለሃብቶችና ተቋማት በተለያየ መንገድ የክ/ከተማውን የልማት እቅድ እንደሚደግፉም ቃል ገብተዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት ቂርቆስ በጉስቁልና እየተጠራች መቀጠል የለባትም፡፡ ትንሻ አዲስ አበባ ናት በማለት ገልፀዋል፡፡ እዚህ የተገኛችሁት ለበጎ እና ለተቀደሰ ተግባር ሌሎችን ለማገልገል ነው ብለው ገልፀዋል፡፡

እንደ ክብርት ከንቲባ አገላለፅ ባለፉት 60/90 ቀናት የሰው ተኮር ተግባራት በእርግጥም ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን አንስተው ለምሳሌ በአንድ አካባቢ በተሰራ ቤት ግንባታ 6 ሰዎችን ከአካባቢው በማንሳት 55 ሰዎች ሚበቃ መኖያ ቤት መሰራት መቻሉን አብራርተዋል፡፡

Share this Post