በመዲናችን አዲስ አበባ ለልማት የተሰጡ 90 ሄክታር መሬት ለረጅም ጊዜያት አጥረው ያቆዩና ወደ ልማት መግባት ያልቻሉ አካላትን የሊዝ ውላቸውን በማቋረጥ መሬቱን ወደ መሬት ባንክ ገቢ በማድረግ ለጨረታ እንዲቀርቡ ወስነናል፡፡

የተሰጣቸውን ውስን የሆነውን የመሬት ሀብት ወደ ስራ በማስገባት ሀገርንም ይሁን የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የሚያግዙ እና ለብዙዎች የስራ ዕድል ይፈጥራሉ ተበሎ የተሰጣቸውን መሬት ወደ ልማት ከማስጋባት ይልቅ ጥቂቶች ምንም ሳይሰሩ ቦታውን እየሸጡ የሚከብሩበት ሁኔታ እንዳይቀጥል ፤የጀመርነውን እርምጃ አጠናክረን እቀጥላለን፡፡

ህብረተሰቡም የጀመርናቸውን የህግ የበላይነትንና የዜጎችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ከጎናችን እንዲሆን ጥሪዬን አቀርባለሁ !!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!

ከንቲባ / አዳነች አቤቤ

Share this Post