15
Jan
2023
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በለሚ ኩራ በዘጠና ቀናት እየተከናወኑ የሚገኙ የመንገድ አካፋይ የአረንጓዴ ልማት፣የአቅመ ደካሞች የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ፣ የእንጀራ ማምረቻ ማዕከል፣የወተት ከብት እርባታ ፣ኮንቬንሽን ማዕከል እንዲሁም አዲሱን የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ህንፃን እና የመንገድ የመሠረተ ልማት ስራ ያለበትን ደረጃ ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም በክፍለ ከተማው በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች በተወሰነላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ለማድረግ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን ያደነቁ ሲሆን በቀሪ ስራዎች ላይም በተሻለ ትጋትና ቁርጠኝነት በመስራት በጋራ የምናስበው ስኬት ላይ መድረስ እንደሚቻል በጉብኝቱ ወቅት ገልጸዋል።
በክፍለ ከተማው እየተገነቡ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች በበጎ ፍቃደኛ ሀገር ወዳድ በሆኑ ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች እንደሆነም በጉብኝቱ በተጨማሪነት ተገልጾል።