10
Mar
2023
በከንቲባ አዳነች አቤቤ ድጋፍ እና ክትትል ሲደረግባቸው የነበሩ የተቋማዊ ሪፎርም የዲጂታል ቴክኖሎጂ መተግበሪያ ዘመናዊ ሕንፃ እና ሌሎች የ90 ቀን ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ዛሬ ይመረቃሉ።
ከሚመረቁት ፕሮጀክቶች መካከል የለሚ ኩራ የቴክኖሎጂ ማዕከል ህንጻ ፥ G+4 የመኖሪያ ቤቶች፣ ሞዴል ጤና ጣቢያዎች፣የውሃና የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ እና መሰል ፕሮጀክቶች ይገኙበታል፡፡
በ 14-05-2013 ዓ.ም ለምረቃ ዝግጁ የነበረው የክፍለከተማ አስተዳደሩ ሕንፃ እና በሕንፃው ውስጥ ዝርጋታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ በሆኑ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች ላይ በተከሰተው እሳት ጉዳት ደርሶ የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡
ይሁን እንጂ በእሳት አደጋው ጉዳት ደርሶበት የነበረው ሕንፃ እና የቴክኖሎጂ ልማት ለሕዝብ በተገባው ቃል መሰረት በአጭር ጊዜ ውስጥ የመልሶ ግንባታ ፥ጥገናና የቴክኖሎጂ መሰረተ-ልማት ዝርጋታው በአፋጣኝ እንዲስተካከል ተደርጎ ለሕዝብ አገልግሎት ዝግጁ ሆኗል።
በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ90 ቀናት የተገነቡ ሁሉም ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች ከመንግስትና ከባለሃብቱ በተገኘ የበጀት ድጋፍ የተገነቡ ናቸው።