ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የC40 የአፍሪካ ክልላዊ ዳይሬክተር ከሆኑት ሚስተር ሃስቲንግስ ቺኮኮ ጋር አዲስ አበባ

በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳድራ ለሽልማት የበቃችባቸውን ስራዎች የመስክ ጉብኝት አካሄዱ፡፡

በጉብኝታቸው የምገባ ማእከል ፤የቀልዝ ምርት የደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀም አምራቾች ተመልክተዋል፡፡

ዛሬ ወደ እናንተ የመጣነው በወጣቶቻችን በድፍረት ተሞክሮ በአለም ደረጃ ስላስከበረን እንዲሁም ተጠቃሚም ስላደረገን ልናመሰግናችሁም ነው ሲሉ ከንቲባ / አዳነች ገልፀዋል፡፡

ያገኘነውን ሽልማት ዝም ብለን እየተኩራራንበት ልንፈነጥዝበት አይደለም ያሉት ከንቲባዋ ልንሰራ እንደምንችል ትጥቅ እንዲሆነን፤ ወኔ እንዲሆነን፤ እንድንነሳሳ፤ የሌማት ትሩፋትን በእርግጥ ለማረጋገጥ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ወደ ውጪ መመልከት አቁመን ወደ ጓዳችን ወደ ጓሮአችን በመመልከት ህዝባችንን በተሟላ ሁኔታ የሚንቀሳቀስበትን ሁኔታ በመፍጠር ኢኮኖሚያዊ ሉአላዊነታችንን ልናረጋግጥ ይገባል ብለዋል፡፡

በዚህ ዘርፍ የተሰማሩት ወጣቶች በላባቸው ሀብት ማፍራት ስለመቻሉ በተግባር አረጋግጠዋል ያሉት የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ስራ አስኪያጅ / እሸቱ በዚህ ዘርፍ ለሚሰማሩ ሌሎች ወጣቶች ከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል::

Share this Post