"ከተማችንን ስማርት ሲቲ (Smart City) ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

የከተማችን አስተዳደር ከተማዋን የሚያዘምንና የሚያሻሽል የቴክኖሎጂ ሲስተምና መሰረተ ልማት በመገንባት እያጋጠመ ያለውን የአገልግሎት ችግሮች እንዲሁም የሌብነትና ሙስና ማነቆዎችን በዘላቂነት ለመፍታት እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡

ዛሬ በአዲስ አበባ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ተጠንቶ በቀረበ ጥናት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂደናል፡፡

በውይይታችንም በጥናቱ ግኝት እና ምክረሃሳብ መሰረት የሁሉንም ባለድርሻ ተቋም ብቃት እና አቅም በመጠቀም የከተማዋን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ መፍትሄ ለመስጠት የጀመርነውን ስራ ስራ አጠናክረን ለመቀጠል አቅጣጫ አስቀምጠናል፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!"

ከንቲባ / አዳነች አቤቤ

Share this Post