ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች በአፍሪካ ህብረት የልማት ኤጀንሲ (The African Union Development Agency) NEPAD ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ናርዶስ በቀለን በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

 

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለአፍሪካ ህብረት የልማት ኤጀንሲ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ናርዶስ የሃገሪቱን የለውጥ እንቅስቃሴ በተለይም በመዲናዋ አዲስ አበባ እየተከናወኑ ያሉ የለውጥና የሪፎርም ስራዎች ስላሉበት ደረጃ ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡

በተለይም በፈተናዎች ውስጥ አልፎ በርካታ የዜጎችን ህይወት የሚቀይር ፤ የከተማችንን ጎስቋላ ገፅታ የሚያድስ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ወ/ሮ ናርዶስ በቀለ በበኩላቸው በሃገሪቱ እየተካሄደ ያለውን የለውጥ እንቅስቃሴ ተስፋ ሰጪ መሆኑን ገልፀው በተመለከቱት ነገር በእጅጉ መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች ዘመናዊ የጥቁር ህዝቦች ኩራት መታሰቢያ የሆነውን የአድዋ ሙዚየምና የማዘጋጃ ቤት ህንፃ እድሳት ስራን ለወ/ሮ ናርዶስ አስጎብኝተዋል፡፡

Share this Post