07
Mar
2022
የአድዋ በአል ለ28 ዓመታት እናት እና አባት አርበኞች በሚኒሊክ አደባባይ የአበባ ጉንጉን ካስቀመጡ በኋላ ጥቂቶቹ ወደ አድዋ አደባባይ በመሄድ ነበር የሚያከብሩት። የባህል ሚኒስትር እና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ትግራይ አድዋ በመሄድ ነበር ሲያከብሩ የቆዩት።
ከባለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ግን ይህ ተቀይሮ አድዋ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት፣ በ100 ሺህ በላይ የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፣ ወጣቶች በነጻነት የአድዋ ጀግኖች መገለጫ የሆኑ አልባሳትን በመልበስ የፈለገ በምኒሊክ አደባባይ፣ የፈለገ በአድዋ አደባባይ፣ ሁለቱም ቦታ ጭምር በመገኘት አድዋን ከፍ በሚያደርግ ሁኔታ ያለስጋት በነጻነት በከፍተኛ ድምቀት ሲከበር ቆይቷል።
ይህ የአድዋን ድል በድምቀት እና በነጻነት የማክበር እድል በሃገሪቱ የመጣው ለውጥ ፍሬ ነው።
ኢትዮጵያ ታፍራ እና ተከብራ ለዘላለም ትኑር !!
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ