146 የፖሊስ አባላትና አመራሮችን በሥነ ምግባር ጉድለት ከሥራ ማሰናበቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ

በሥነ ምግባራቸው ፖሊስን የማይመጥኑና ጥፋት አጥፍተዋል ያላቸውን 146 የፖሊስ አባላትና አመራሮችን ከሥራ ማሰናበቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።የአዲስ አበባ ፖሊስ ባለፉት 6 ወራት ያከናወናቸውን የወንጀል መከላከልና ምርምራ ተግባራትን አፈፃፀም አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የአዲስ አበባ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ በአስቸኳይ ጊዜ አዎጁ በርካታ ተግባራት እንደተከናወኑ ተናግረዋል።በተደረገ ፍተሻና ብርበራም 47 ቦምብ፣ 8 ፈንጂዎች፣ 113 ክላሽን ኮቭ ጠብመንጃ፣ 422 ልዩ ልዩ ሽጉጦች ከ17 ሺሕ በላይ የክላሽ፣ ከ8 ሺሕ በላይ የሽጉጥ ጥይቶች፣ 2 ሺሕ 901 የብሬን እና 8 የመትርዬስ እና 183 የልዩ ልዩ የጦር መሳሪዎች ጥይቶችን መያዝ እንደተቻለም ገልጸዋል፡፡

ከእነዚህ የጦር መሳሪያዎች በተጫማሪ 57 የጦር መሳሪያ መነፅር፣ 2 የጦር መሳሪያ ኮምፓስ፣ 64 ወታደራዊ የመገናኛ ሬድዮ፣ 3 የመገናኛ ሬዲዩ ቻርጀር፣ 6 ጂፒኤስ እና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁስ ከእነተጠርጣሪዎቹ ተይዘው አስፈላጊው ምርመራ የማጣራት ሥራ እየተሰራ ሲሆን ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውሩን ለመከለከልና ህገ-ወጦችን ለህግ የመቅረቡ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል ተብሏል፡፡

 

 

 

Share this Post