17ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ማጠቃለያ የባህል ፌስቲቫል መክፈቻ ስነ ስርዓት *******************

 

የሁሉም የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች በአብሮነት በፍቅር በአንድነት በጋራ የሚያከብሩት የጋራ እሴት የሚፈጥሩበት17ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአል በመስቀል አደባባይ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በአሉ በከተማ ጀረጃ ከህዳር አንድ ጀምሮ በክ/ከተሞች በመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች በፖናል ውይይት በተለያዩ መርሀ ግብሮች ሲከበር የቆየ ሲሆን ዛሬ በማጠቃለያ መርሀ ግብሩ የሁሉም ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች የተውጣጡ ተወካዮች የባህል ትርኢት የምግብና የባህል አልባሳት አውደ ርዕይ ለታዳሚያን እያቀረቡ ይገኛል።

በእለቱ ከሁሉም የክልል ምክርቤት አፈጉባኤዎች የፌደሬሽን ምክር ቤት ተወካዮችና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ተገኝቸውበታል።

Share this Post