30 ሺህ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ፤ መምህራንና የትምህርቱ ማህበረሰብ አካላት የሚሳተፉበት ዘመቻ ተጀመረ

 

በአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስተባባሪነት ከ30 ሺህ በላይ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ፤ መምህራን፣ የትምህርቱ ማህበረሰብ አካላት "በትምህርት ልማት ግምባር " በሚል መሪ ቃል የሚሳተፉበት ዘመቻ የዘማችአርሶአደሮችና የሚሊሻ ቤተሰቦችን የደረሰ ሰብል በመሰብሰብ የተጀመረ ሲሆን በዚህም ደጀንነታቸዉን አሳይተዋል ።

ዛሬ የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት በኦሮሚያ ክልል የፊንፊኔ ዙሪያ በበረክ ወረዳ ግራር በረክ ቀበሌ አካባቢ በይፋ በተጀመረው ዘመቻ ከ3ሺህ በላይ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ፤ መምህራንና የትምህርቱ ማህበረሰብ አካላትና የፖሊስ አባላት ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን 15 ሄክታር የደረሰ የስንዴ ሰብል ሰብስበዋል ።የአገር ሉአላዊነትን ለማስከበር ልጆቻቸውን ፣ ቤተሰቦቻቸውን ፤ ክረምት ከበጋ የለፉበትን ማሳ ትተው ወደ ግምባር የዘመቱ አርሶአደሮችን እና ሚሊሻዎችን የመኸር ሰብል መሰብሰብ፤ ቤተሰቦቻቸውን ማገዝ ትልቅ ክብር ነዉ ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፤ በሁሉም የጦር ግምባሮች ያሳካናቸዉን ድሎች በኢኮኖሚው ዘርፍም መድገም ይገባናል ነዉ ያሉት ።ዘመቻው በቀጣይም በደም ልገሳ ፤ በአካባቢ ጥበቃና የዘማች አርሶ አደሩን የመኸር ወቅት ሰብል በመሰብሰብ እና ቤተሰቡን በማገዝ በተለያዩ አካባቢዎች የሚቀጥል ይሆናል ።

Share this Post