45 ዶክተሮች እና የህክምና ባለሙያዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ሙያዊ ድጋፍ ለመሰጠት ሽኝት ተደረገላቸው ። "ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ"!! በአዲስ አበባ ከተማ ካሉ ሆስፒታሎች የተውጣ...

45 ዶክተሮች እና የህክምና ባለሙያዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ሙያዊ ድጋፍ ለመሰጠት ሽኝት ተደረገላቸው ። "ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ"!! በአዲስ አበባ ከተማ ካሉ ሆስፒታሎች የተውጣጡ የጤና ቢሮ ኃላፊው ዶክተር ዮሀንስ ጫላን ጨምሮ 45 ዶክተሮች እና የህክምና ባለሙያዎች የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ በዛሬው ዕለት በመስቀል አደባባይ አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል ። ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቀነአ ያደታ ፣የሀገር ሽማግሌዎች እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ለባለሙያዎቹ አሸኛኘት ተደርጓል ። የህክምና ባለሙያዎቹ ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት መድሀኒቶች እና የህክምና በቁሳቁሶችን ይዘው ተጉዘዋል። ከዚህ ቀደም በሁለት ዙሮች ከከተማዋ የተለያዩ ሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች የተውጣጡ ዶክተሮች እና የህክምና ባለሙያዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ ወደ ትግራይ ክልል መጓዛቸው ይታወሳል ።

Share this Post