11
Oct
2022
6ኛው የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን መክፈቻ ስነ-ስርዓት የጋራ ስብሰባ መካሄድ ጀምሯል።
በዚህም 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ሥነ-ስርዓት ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የ2015 ዓ.ም ዋና ዋና የመንግስት አቅጣጫዎችን የሚያመላክት ንግግር እያደረጉ ይገኛል።
በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የሁለቱም ምክር ቤቶች አባላት ተገኝተዋል።
በመርሐ ግብሩ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።