01
Mar
2023
የተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት የትምህርት ሚኒስትሮች ፣ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ኃላፊዎች ፣ የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና የትምህርት ኮሚሽነሮች እንዲሁም የተለያዩ ሃገራት የምገባ ኤጀንሲዎች በተገኙበት በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ አክብረናል::
ትላንት ስንጀምረው ቀላል ይመስል የነበረው የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ዛሬ ላይ አድጎ እና አለምአቀፍ እውቅናን አግኝቶ የተለያዩ ሃገራት ልምድ የሚወስዱበት ስራ በመሆኑ እጅግ ደስ ይለናል::
አሁንም ትውልድ የመገንባት ስራችን በማጠናከር ለተማሪዎቻችን ምግብ ብቻ ሳይሆን ፍቅርንም እየሰጠን ሃገሩን የሚወድ ጠንካራ ዜጋ የማፍራት ስራችንን እንቀጥላለን::
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ