31
Mar
2022
የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚኒስትሩ ዶ/ር በለጠ ሞላ በየተባበሩት አረብ ኤመሬትስ ዱባይ ላይ የተዘጋጀውን የአለም መንግስታት ሰሚት (World Government Summit 2022) እና የሴቶች ተሳትፎ በመንግስት አመራርነት (Women in Government Summit) ላይ ተሳትፈዋል።
ከመጋቢት 19 ፣ 2014 ዓ.ም ጀምሮ በዱባይ ኤክስፖ ማዕከል የተካሄደው ይህ አለማቀፍ ሰሚት ከተለያዩ ሃገራትን የተውጣጡ 1500 በላይ የመንግስታት መሪዎችና አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅት አመራሮች በጋራ ወቅታዊ በሆኑ ጉዳዮች ማለትም በኢኮኖሚ፣ በከተማ አስተዳደር ፣ በማህበራዊ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በኢንቨስትመንት፣ የሴቶች ተሳትፎ በመንግስት አመራርነት፣ በኮምንኬሽን ዙሪያ የተማከሩበት መድረክ ነበር።
በተጨማሪም ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከየተባበሩት መንግስታት የካፒታል ልማት ፈንድ ኤግዘኪውቲቭ ዳይሬክተር ክብርት ፕሪቲ ሲንሃና ከየተባበሩት አረብ ኤመሬትስ የማህበራዊ ልማት ሚኒስቴር ክብርት ኤሳ ብሁመይድ ጋር የሁለትዮሽ ትብብር ስራዎችን የጋራ ለመስራት ውይይቶችንም አድርገዋል። በተጨማሪም በዱባይ አክስፖ ማዕከል የኢትዮጵያ እንዲሁም የሌሎች ሃገራት ፓቪሊዮን የጉብኝት አካሂደዋል።